†✝† እንኩዋን ለጥንተ በዓለ ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) በሰላም አደረሳችሁ †✝†
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ
የጌታችን ዓበይት በዓላቱ 2 ጊዜ (ማለትም ጥንተ በዓልና የቀመር በዓል ተብለው) ይከበራሉ:: ዛሬም ከ1,973 ዓመታት በፊት አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ መውረዱን እናስባለን::
††† ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
+ቸር አምላክ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሲል
*ከልዑል ማዕርጉ ወርዶ:
*በማሕጸነ ድንግል ተጸንሶ:
*በኅቱም ድንግልና ተወልዶ:
*ከኃጢአት በቀር በግዕዘ ሕጻናት አድጐ:
*በ30 ዘመኑ ተጠምቆ:
*ቅድስት ሕግ ወንጌልን አስተምሮ:
*በፈቃዱ ሙቶ:
*በባሕርይ ስልጣኑ ተነስቶ:
*በአርባኛው ቀን ያርጋል::
+ታዲያ ደቀ መዛሙርቱን የቅዱስ መንፈሱን ጸጋ ተስፋ እንዲያደርጉ ነግሯቸው
ነበርና በተነሳ በ50ኛው ቀን: በዐረገ በ10 ቀን ተስፋውን ፈጸመላቸው::
+እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዶሮ ጫጩቶቿን በክንፎቿ እንድትይዝ
በአንድ ላይ ሰብስባ ለክብረ መንፈስ ቅዱስ አብቅታቸዋለች:: 120ው ቤተሰብ
ከጌታችን እናት ጋር ሲጸልዩ መንፈስ ቅዱስ በአውሎ ንፋስ አርአያ ወርዶ
በአምሳለ እሳት አደረባቸው::
+ቅዱሳን ሐዋርያት ፈሪዎች የነበሩ ደፋሮች: አሮጌ ሕሊና የነበራቸው
ሐዲሶች ሆኑ:: በአዕምሮ ጐለመሱ: ቁዋንቁዋ ተናገሩ: ምሥጢርም
ተረጐሙ:: በቅጽበትም ብሉይ ከሐዲስ በልቡናቸው ውስጥ ተሞላ::
+ሐዋርያቱ ቅዱስ መንፈስን ተቀብለው ዓለምን በወንጌል ዕርፈ መስቀል
አርሰዋል:: አልጫውን ዓለም ጨው ሆነው አጣፍጠዋል:: ሳይሳሱም
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተዋል::
"ኪያሁ መንፈሰ ነሢኦሙ ለለአሐዱ:
ሐዋርያት ለሰቢክ አሕጉራተ ዓለም ዖዱ:
ሰማዕትኒ ለሕማም ነገዱ::" እንዳለ ደራሲ::
+በዚህ ቀን 2 ነገሮች በትኩረት ይነገራሉ:-
1."የመንፈስ ቅዱስ የባሕርይ አምላክነት:-"
*እርሱ ከአብ የሠረጸ: ቅድመ ዓለም የነበረ: በባሕርይ ስልጣኑ ከአብና
ከወልድ ጋር እኩል የሆነ: የራሱ ፍጹም አካል ያለው ፍጹም አምላካችን
ነውና::
2."ቅድስት ቤተ ክርስቲያን:-"
*አብ ያሰባት: ወልድ በደሙ የቀደሳት: መንፈስ ቅዱስ በጸጋው ያጸናት
የክርስቲያኖች አማናዊት አንድነት: አንድም ቤት ናትና:: ዛሬ በጉባዔ
ተመስርታለች::
=>+"+ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው
አብረው ሳሉ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ድምጽ መጣ::
ተቀምጠው የነበሩበትንም ቤት ሁሉ ሞላው:: እንደ እሳትም የተከፋፈሉ
ልሳኖች ታዩአቸው:: በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጡባቸው:: በሁሉም
መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው:: መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ
ልሳኖች ይናገሩ ጀመር:: +"+ (ሐዋ. 2:1-4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

አስተያየቶች