በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
የእመቤታችን ወዳጆች ሆይ እንኳን ለንጽሕተ ንጹሐን ለቅድስተ ቅዱሳን ለድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ፅዮን ማርያም (አክሱም ፅዮን ) ታላቅ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን ! አደረሳችሁ!
ወበዛቲ እለት ህዳር 21 ቀን የእስራኤላውያን መመኪያ በእመቤታችን ስም የተሰየመችው ታቦተ ጽዮን ዳጐን በተባለው ጣኦት ላይ ኃይሏን ክብሯን የገለጸችበት ቀን ነው::

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመፅሐፍ ቅዱስ በጥቂቱ
...............................................................................................
ድንግል ሆይ በቤተ ልሔም ካንቺ የተለደውን መወለድ በጨርቅ የተጠቀለለውንም አድግና ለህም በብርድ ወራት እስትንፋስን ያሟሟቁትንም አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ በሄርድስ ዘመን ከርሱ ጋራ ከሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋራ ወሰደዱን አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ከዕይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፡፡ ድንግል ሆይ ርኃቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ፡፡ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥእን አሳስቢ፤ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፍት አሳስቢ፡፡
የልመናዋ ክብር ፍጹም የሆነ፤ የረድኤትዋ ሀብት ጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚመላ፤ የተወደደ የልጅዋ ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን!!!

አስተያየቶች