+++“ድነሃል ወይስ አልዳንክም?”+++
=================
ከ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖቴ ገፅ
----
ብጹዕ ወ ቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በአንድ መጽሐፋቸዉ እንዲህ ይላሉ፡፡
----
አንድ ወጣት ልጅ እንዲህ ብሎ ጠይቆኛል፤“አንድ ሰዉ ድነሃል ወይስ አልዳንክም?” ብሎ ቢጠይቀኝ መልሴ ምንድነዉ? መጀመሪያ ይሄ ሰዉ እዉነተኛ ኦርቶዶክስ እንዳልሆነ ማወቅ አለብህ፡፡ በእርግጠኝነት ይሄ ሰዉ ፕሮቴስታንት ነዉ፤ወይንም ቢያንስ በፕሮቴስታንታዊ ባህል ዉስጥ ነዉ የሚኖረዉ፤ባህሉም የፕሮቴስታንት ነዉ፡፡ ከዚህ በፊት የተቀበልካቸዉን ምስጢራትንና ጥምቀትን እንደ ምንም ቆጥሮ፣ በሃይማኖትህ ላይ ጥርጥር ለመሙላት በመሞከር፣ባለፈዉ የሕይወት ዘመንህ ሁሉ አሕዛብ እንደነበርክ አድርጎ እንደ ገና እመንና ዳን ሊልህ ነዉ፡፡ ይሄ ሰዉ በፍጹም ኦርቶዶክስ ሊሆን አይችልም፤አነጋገሩም ይገልጠዋል፡፡
ለማንኛዉም እንዲህ ብለህ ልትመልስለት ትችላለህ፤ "በጥምቀት ከአዳም የዉርስ ኀጢአት ድኜያለሁ፤ይሄ ድኅነት የሚገኛዉ በደመ ክርስቶስ የቤዛነትንና የድኅነት ኀይል ነዉ፡፡ ነገር ግን የመጨረሻዉ ድኅነት በስጋ ስንለይ የሚገኝ ነዉ፡፡ አሁንም በዉጊያ ላይ ነን “መጋዳላችን ከደምና
ከስጋ ጋር አይደለምና፣ከአለቆችና ከስልጣናት ጋር ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዢዎች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳዊያን ሰራዊት ጋር እንጂ፡፡” (ኤፌ.6፣12) ይሄንን ዉጊያ ድል ስናደርግና ስናሸንፍ ድኅነትን እናገኛለን…”
በስጋ እስካለን ድረስ “ድል ነስተናል፤ድኅነትን አግኝተናል” ልንል አንችልም፡፡
ስለዚህ ቅድስት ቤተክርስቲያን የቅዱሳንን ልደት አታከብርም ወይም የተጠመቁበትን ዕለት ይልቁንም ከዚህ ዓለም የተለዩበትን ወይንም መስዋዕት የሆኑበትን ቀን ታከብራለች እንጂ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላልና፤“ዋነኞቻችሁን አስቡ፣የኑሮአቸዉንም ፍሬ እየተመለከታችሁ
በእምነታቸዉ ምሰሉአቸዉ፡፡” (ዕብ.13፣7)
ስለዚህ በቅዳሴ ላይ የቅዱሳንን መታሰቢያ እናደርጋለን፤በእምነት ፍጹማን የሆኑትንና ሕይወታቸዉን በእምነት የፈጸሙትን፣በአጸደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ሁሉ እናስባለን፡፡ ይሄም የታላቁ አባ መቃርስን ከዚህ ዓለም መለየት እንዳስታዉስ ያደርገኛል፤ ነፍሱ ከስጋዉ ተለይታ ስትሄድ፣ “መቃርስ፣አንተ ድነኸል” እያሉ አጋንንት ነፍሱን
አሳደዷት፤ ነገር ግን ገነት እስከሚገባ ድረስ፣ ”ጌታ ጸጋ ድኛለኹ”አላላቸዉም ነበር…!
አባታችን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ነገረ ድኀነትን አስመልክቶ ለፕሮቴስታንቶች መልስ ከሰጡበት የተወሰደ

አስተያየቶች